loader image

ሂጅራ ባንክ ወደ ትርፍ ተሻገረ!

ሂጅራ ባንክ ከብሄራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት በሀገራችን ሙሉ በሙሉ ሸሪዓውን መሠረት ያደረገ የወለድ ነጻ አገልግሎት ለመስጠት በነሐሴ 29 2013 ሥራውን መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ባሳለፈው የአንድ ዓመት ከከአስር ወር ጉዞ በሀገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ታሪክ አመርቂ የዕድገት መጠንን በማስመዝገብ በስኬት ጎዳና እየገሰገሰ ይገኛል፡፡ በተጠናቀቀው የ 2022/23 የበጀት ዓመት 162% (አንድ መቶ ስድሳ ሁለት በመቶ) የትርፍ መጠን ዕድገትን ጨምሮ በርካታ አንኳር ስኬቶችን ማስመዝገቡን ሲያበስር በላቀ ደስታ ነው፡፡
በበጀት ዓመቱ ካስመዘገባቸው አመርቂ ስኬቶቻችን መካከል ዋና ዋና የሆኑትን እንደሚከተለው ቀርቧል፦
1. ትርፋማነት፡ ሂጅራ ባንክ ሥራ በጀመረ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ትርፍ በማስመዝገብ በዘርፉ ያልተለመደ ስኬት ሊቀዳጅ ችሏል።ሂጅራ ባንክ በበጀት ዓመቱ ይህን ስኬቱን ያስመዘገበው በሀገሪቱ የወለድ ነጻ ባንክ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን በማለም ባረቀቀው የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድና ተፈጻሚነት እንዲሁም ከጅምሩ በተከተለው የኢንቨስትመንት አቅጣጫ ነው።
2. አመርቂ እድገት፦ ሂጅራ ባንክ ሥራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ በህብረተሰባችን ዘንድ ጠንካራ እምነት በመጎናጸፍና ተመራጭ ባንክ በመሆን አምስት ቢሊዮን (5,000,000,000) ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ችሏል፡፡ ይህም ካለፈው የበጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር በ273%(ሁለት መቶ ሰባ ሦስት በመቶ) እድገት ያስመዘገበ ሲሆን ለዚህም ስኬቱ የሂጅራ ባንክ ቤተሰቦቹን ከልብ ያመሰግናል፡፡
3. ሠፊ የደንበኛ መሠረትና የቅርንጫፍ ማሥፋፋት፦ ሂጅራ ባንክ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት መርህን በመከተሉ በ2022/2023 የበጀት ዓመት የደንበኞቹን ብዛት በ122% (አንድ መቶ ሀያ ሁለት በመቶ) እንዲሁም የቅርንጫፎቹን ብዛት ደግሞ 80% (ሰማንያ በመቶ) ማሳደግ መቻሉ የስኬቱ ጉልህ ማሳያ ነው።

4. ጠንካራ የሀብት መሠረት፦ ሂጅራ ባንክ ስኬቱን በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለማጽናት በመትጋት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የሀብት ምጣኔውን በ207% (ሁለት መቶ ሰባት በመቶ) በማሳደግ ሰባት ነጥብ አንድ ቢሊዮን (7,100,000,000) ብር ለማድረስ ችሏል።
5. ሂጅራ ባንክ አስተማማኝ፥ ቀዳሚና የላቀ የባንክ ቴክኖሎጂ ባለቤት፦ ሂጅራ ባንክ በወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ በቴክኖሎጅ ፈር ቀዳጅ ለመሆን ባለው የጸና እምነት በሀገራችን አዲስ የሆነ፣ ሙሉ ለሙሉ የወለድ ነጻ ባንኮችን ብቻ ታሳቢ ተደርጎ የበለጸገ፣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከሸሪዓ መርህ ጋር ሙሉ በሙሉ የተጣጣመ፣ ለዚህም ከዓለም አቀፉ የምዘና ተቋም (Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions-AAOIFI ) በየዓመቱ ማረጋገጫ የሚሰጠው፣ በዓለማችን ከ165 በላይ የሆኑ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች የሚገለገሉበትን የአይማል ኮር ባንኪንግ ሲስተም (iMAL Core banking) ከ 18 የሚበልጡ ሞጁሎችን በአጭር ጊዜ ተግብሮ በሥራ ላይ በማዋል ቀዳሚ መሆን የቻለ ባንክ ነው።
በተጨማሪም የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የመጨረሻውን ደረጃ ማለትም ኦምኒ ቻናል (Omni Channel) አገልግሎትን ከተገበሩ የሀገራችን ሁለት ባንኮች አንዱ መሆን ችሏል።
6. ተጨማሪ አዳዲስ የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ፦ ከጅምሩ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የወለድ ነጻ ባንክ ሆኖ የተቋቋመው ሂጅራ ባንክ እስካሁን ሲሰጣቸው ከነበሩት የወለድ ነጻ አገልግሎቶች በተጨማሪ ለዘንድሮ የበጀት ዓመት አዳዲስ የወለድ ነጻ አገልግሎቶችን ለህብረተሰባችን ለማብሰር ዝግጅቱን አጠናቋል።
ከላይ የጠቀስናቸውን እና እዚህ ያልተገለጹ ስኬቶቹን በቀጣይነት ለማጽናት እንዲሁም ባንካችንን በተደላደለ መሠረት ላይ ለማስቀመጥ ከዚህ ቀደም አክሲዮን የመግዛት እድሉ ላመለጣቸውና አክሲዮን እንዲሸጥላቸው በየዕለቱ እየጠየቁ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳግም እድሉን ለመስጠት በማሰብ ለነባር የአክሲዮን አባላት፣ ለደንበኞችና ለመላው ህብረተሰብ በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች አዲስ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን ሲያበስር በላቀ ደስታ ነው።
ሂጅራ ባንክ እነኚህን ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ማስመዝገብ የቻለው ባጠቃላይ የባንክ ኢንዱስትሪው በከፍተኛ ዉድድር ላይ ባለበትና እንደ ሀገር በኢኮኖሚው ዘርፍ ከፍተኛ ጫና በሚስተዋልበት ወቅት መሆኑ ስኬቱን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል።
ለዚህ ስኬት ከፍተኛውን ሚና የነበራችሁ ክቡራን የባንካችን ደንበኞች፥ ባለአክሲዮኖች፥ የቀድሞና የአሁን የቦርድ አባላት፥ የባንኩ የሸሪዓ አማካሪዎች፣ የባንኩ አስተዳደሮች፥ ትጉሃን ሠራተኞች፥ የባንኩ ፕሮሞተሮች እና ሰፊው የሂጅራ ባንክ ቤተሰቦች ናችሁና እኔም በራሴና በሒጅራ ባንክ አመራር ስም ለባንካችን ስኬት እስካሁን ላደረጋችሁት አስተዋፅኦ ባንካችን ከልብ ያመሰግናል፡፡
በድጋሜ ለማስተዋስ ያክል በምሥረታ ወቅት የባለአክሲዮን ድርሻ አባልነት ዕድልን ያላገኛችሁ የሂጅራ ባንክ ቤተሰቦቻችን ስኬታማ ጉዞን እያደረገ ባለው ባንካችን ባለድርሻ እንድትሆኑ ልዩ የአክሲዮን ሽያጭ ያዘጋጀን መሆኑን አየገለጽን በአገልጋይነት ስሜት ተግቶ ከሚሠራው ሂጅራ ባንክ ጋር አብራችሁ እንድትሠሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ሰኔ 30 ቀን 2015 – አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

1 thought on “ሂጅራ ባንክ ወደ ትርፍ ተሻገረ!”

  1. አልሐምዱሊላህ በጣም ደስ ይላል በርቱ ። ምንም እንኳን ሁሉንም ነገር ባሟላም እስከአሁን ሰርትፍኬትባላገኝም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top