loader image

ሂጅራ ባንክ ለሐጅና ዑምራ ተጓዦች “ሐረመይን” የተሰኘ ልዩ የቁጠባ አገልግሎት አስጀመረ

ሂጅራ ባንክ ለሐጅና ዑምራ ተጓዦች “ሐረመይን” የተሰኘ ልዩ የቁጠባ አገልግሎት አስጀመረ:: 50% የብድር አቅርቦት ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ፡፡

ለማህበረሰቡ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ግንባር ቀደም በመሆን እየሰራ የሚገኘው ሂጅራ ባንክ ሐረመይን የተባለ አዲስ የቁጠባ ሂሳብ በዛሬው ዕለት መጋቢት 03 ቀን 2015 ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በማቅረብ አስተዋወቀ፡፡

ከአምስቱ የኢስላም መዕዘናት አንዱ የሆነው ሐጅ አንድ ሙስሊም ጤናማ አዕምሮ ካለው፣ ለአካለ መጠን ከደረሰ እንዲሁም አካላዊ እና ቁሳዊ አቅሙ ከተሟላለት በህይወት ዘመኑ አንዴ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ባንካችን ይህንን የደምበኞቹን የህይወት ዘመን ህልም ለማሳካት እና የደምበኞቹን የአቅም ውስንነትን ለመፍታት ታሳቢ በማድረግ ሁለት አይነት ልዩ የቁጠባ አማራጮችን አቅርቧል፡፡

1.  ሐረመይን ወዲዓ የሐጅና ዑምራ ቁጠባ ይህ የቁጠባ አይነት የተለመደ የወዲአ ቁጠባ ሲሆን የሐጅ እና ዑምራ ጉዞ ማድረግ ለሚፈልጉ ደንበኞችን ቅድሚያ በመቆጠብ ለጉዞ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያጠራቅሙበት መደበኛ የቁጠባ አገልግሎት ነው፡፡

2.  ሐረመይን በቋሚነት የሚቆጠብ የሐጅና ዑምራ ቁጠባ ደንበኛው ሂሳብ ሲከፍት የቁጠባ ጊዜውን እና የገንዘብ መጠኑን ወስኖ በየወሩ በቋሚነት በመቆጠብ ለሐጅና ዑምራ ጉዞ የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን እስከ 50% ደንበኛው ሲቆጥብ ባንኩ በዉሉ መሰረት ቀሪውን 50% የብድር አቅርቦት ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ/ በቀርደል ሀሰን/ የሚያበድርበት ልዩ የቁጠባ አገልግሎት ነው። ደምበኞች ቋሚ ቁጠባቸውን ከ 1-5 ዓመት ብቻ የሚጠበቅባቸውን መጠን በመቆጠብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሐጅ ማድረግ ይችላሉ፡፡

እነዚህ ሁለት ዓይነት የሐጅ የቁጠባ ሂሳቦች ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች የሐጅና ዑምራ ጉዞ በቀላሉ ማድረግ እንዲችሉ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል፡፡

ሂጅራ  ባንክ – ጉዞ ወደ ብሩህ ተስፋ!

One Reply to “ሂጅራ ባንክ ለሐጅና ዑምራ ተጓዦች “ሐረመይን” የተሰኘ ልዩ የቁጠባ አገልግሎት አስጀመረ”

Ahmed Abdulkadier, April 5, 2023

Alhamdulillah, I would like to Thanks for giving this chance for our oma..!!

Leave A Comment