
ሂጅራ ባንክ አክሲዮን ማህበር
የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ህግ አንቀጽ 366(1)፣367(1)፣ እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 17 መሠረት የሂጅራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ይካሄዳል።
በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል።
1.ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፦ አ/አ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01፣ የቤት ቁጥር 10/4
ድረ-ገጽ- https://hijra-bank.com/
1.2 የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፦ MT/AA/3/0052401/2013
1.3 የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ፦ 1,932,521,000.00
1.4 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፦ 1,932,521,000.00
- የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1 የዳይሬክተሮች ቦርድ የጥቆማና አስመራጭ ጊዜያዊ ኮሚቴ መሰየም፣
2.2 እ.ኤ.አ 2024/2025 የተፈጸሙ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና አዳዲስ አክሲዮኖችን ማጽደቅ፣
2.3 የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማ እና ምርጫ አፈጻጸም መመሪያ ማጽደቅ፣
2.4 እ.ኤ.አ የ2024/2025 ሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
2.5 እ.ኤ.አ የ2024/2025 ሂሳብ ዓመት የውጪ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
2.6 እ.ኤ.አ. በ2024/25 ሂሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
2.7 እ.ኤ.አ 2025/26 ሂሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር መሾም፣
2.8 የዳይሬክተሮች ቦርድ 2024/25 ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያን እና የ2025/26 ወርሃዊ አበል መወሰን፣
2.9 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማከናወን - የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ
3.1 የባንኩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል
ማሳሰቢያ
✅በጉባዔው ላይ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ በማህበሩ ዋና መ/ቤት አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾም የሚችሉ ሲሆን ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ በጉባዔው መካፈል እና ድምጽ መስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን
✅በብሄራዊ ባንክ ኮርፖሬት አስተዳደር መመሪያ ቁ. SBB 91/2024 አንቀጽ 20.3 መሰረት የዳ/ቦርድ አባላት እና ማንኛውም የባንኩን ሠራተኛ መወከል የማይቻል መሆኑን እንዲሁም አንድ ባለአክሲዮን በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።
✅ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ የዲጂታል/ፋይዳ መታወቂያ፣ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ። እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆናችሁና የውጭ ሀገር ዜግነት ያላችሁ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዛችሁ መቅረብ እንዳለባችሁ በአክብሮት እንገልጻለን።
የሂጅራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave A Comment