loader image

አገልግሎቶቹ ዘካት፣ ሰደቃ እና ወቅፍ የሚባሉ ሲሆን አገልግሎቶቹም በኢስላሚክ ኢኮኖሚክስ አረዳድ በማህበረሰቡ ዘንድ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን በማስፈን፣ የተከማቸ ሃብትን ለተቸገሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በማከፋፈል ህበረተሰቡ ዘንድ የኢኮኖሚ እኩልነት እንዲሰፍን እንዲሁም ድህነት እና ችግርን ለመቅረፍ እንዲያስችል በማሰብ መዘጋጀታቸውን የባንካችን ተ/ ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ቀኖ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል፡፡
ዘካት ከእስልምና እምነት ማዕዘናት አንዱ ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች የሚያፈሩት ሀብት በአስተምርሆቱ መሰረት ከተቀመጠው መጠን በላይ ሲሆን ከሃብታቸው ላይ ለአቅመ ደካሞች የሚውል ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ የእምነቱ ቁልፍ አካል ነው፡፡ በተጨማሪም ሰደቃ እና ወቅፍ ማንኛውም የማህበረሰብ አካል ካለው ንብረት ላይ የተቸገሩትን በመርዳት ወንድማማችነትና የማህበራዊ ትስስርን የሚያጠነክሩ አገልግሎቶች ሲሆኑ ወቅፍ በተለየ ሁኔታ ዘላቂ የማህበረሰብ ግንባታ ላይ በማተኮር ህበረተሰቡን ሊያገለግሉ የሚችሉ ተቋማት ግንባታ ላይ የሚያተኩር አገልግሎት ነው፡፡

Leave A Comment