
ሂጅራ ባንክ በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ የግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንስ ሽልማት GIFA ተሸለመ፡፡
(መስከረም 3፣ 2023) ሂጅራ ባንክ ሴኔጋል፣ ዳካር በተካሄደው የ2023 የግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንስ ሽልማት ስነስርዓት በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ የአመቱ ሻምፒዮን በመሆን ተሸለመ።
የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ተወካዮች፣ ሚንስትሮች፣ አምባሳደሮች እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተካፈሉበት በዚህ በ13ኛው ግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንስ የሽልማት ስነ ስርዓት ባንኩ ይህንን አስደናቂ ሽልማት ሊያገኝ የቻለው በአዲስ አቀራረብ በኢስላማዊ ፋይናንስ ዘርፍ ሥነ ምግባራዊ እና አካታች የፋይናንስ አገልግሎቶችን ከሸሪዓ መርሆች ጋር በማጣጣም ዲጂታል ባንኪንግ መፍትሄዎችን በአጭር ጊዜ ለደንበኞቹ በማቅረብ በተከታታይ ባደረገው ጥረትና የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ ባሳየው ከፍተኛ ቁርጠኝነት ነው።
የሂጅራ ባንክ የልዑካን ቡድን አባልና የባንኩ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሀሰን መሐመድም በዕለቱ ፓነሊስት በመሆን ለነበራቸው ተሳትፎ ዕውቅና ተሰቷቸዋል።
እ.ኤ.አ.ከ13 ዓመት በፊት በ 2011 በኤድቢዝ ኮርፖሬሽን የተመሰረተው የኢስላሚክ ባንክ እና ፋይናንስ ድጋፍ አካል የሆነው GIFA ኢስላማዊ ባንክን እና ፋይናንስን በማስተዋወቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱና በየመስካቸው የላቀ ስኬት ላሳዩ መንግስታት፣ ተቋማት እና ግለሰቦችን እንዲሁም ምርጥ ተሞክሮዎችን እውቅና የሚሰጥ በጣም የተከበረ መድረክ ነው፡፡ GIFA ከዓለም የኖቤል ሽልማት ቀጥሎ ሁለተኛው ዕውቅ የሽልማት መድረክ ነው:: የኢንዱስትሪው አካላት……..
….የኢንዱስትሪው አካላት ለላቀ ደረጃ እንዲጥሩ እና አወንታዊ ለውጥ እንዲያመጡ ማበረታታትን አላማው አድርጎ የተነሳው ይህ ድርጅት በየዓመቱ በኢስላማዊ ባንክ እና ፋይናንስ ልማት ላበረከቱት ልዩ አስተዋፅዖ በዓለም ዙሪያ ላሉ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና ይሰጣል።
GIFA ብቸኛው የአለም ኢስላማዊ ፋይናንስ ሽልማት ስነስርዓት እንደመሆኑ፣ የGIFA አሸናፊዎች ከሁሉም የአለም ማዕዘናት፣ ከአሜሪካ እስከ ኢንዶኔዥያ፣ ከዩኬ እስከ ካዛኪስታን እና ምስራቅ አውሮፓ ይመጣሉ። ሁሉንም የኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት ከፖለቲከኞች ጀምሮ በየዘርፉ የመሪነት ሚና የተጫወቱ ምሁራንን ያካተተ ሽልማት ነው፡፡
ሂጅራ ባንክ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ምርጥ ኢስላሚክ ሪቴይል ባንክ በመባል ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ከዩኬህ አስደናቂ ጉዞ ላይ እምነት ለጣሉብን ውድ ደንበኞቻችን፣ አጋሮቻችን፣ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋናችንን እያቀረብን የናንተ የማያወላውል ድጋፍ እና ትብብር ለዚህ ትልቅ ምዕራፍ ላይ እንድንደርስ አስችሎናል። የሂጅራ ባንክ ቦርድ አባላት፤ የሸሪአ አማካሪዎች፣ የአክሲዮን ባለቤቶች፣ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ታታሪዎቹ ሰራተኞቻችን ይህ ስኬት ያለእናንተ ያላሰለሰ ጥረት እና ቁርጠኝነት ሊሳካ አይችልም ነበር።
ይህንን አስደናቂ ስኬት ስናከብር፣ የማህበረሰባችን ልዩ ፍላጎቶችን የሚያሟሉ ልዩ የዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ባለን ቁርጠኝነት እንደምጸና፤ እንከን የለሽ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ሸሪዓ ህግን መሰረት ያደረጉ የባንክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ደንበኞቻችንን የሚያግዙ እና ዘመኑን የሚመጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ማቅረብ እና ማደስ እንቀጥላለን፤ በኢትዮያ ወለድ አልባ የባንክ ዘርፍን ወደፊት ለማራመድ በተለይ ደግሞ በዲጂታል ባንክ ዘርፍ አለም ወደደረሰበት ደረጃ ለማምጣት ጠንክረን እንሰራለን፡፡ ለማያወላውል ድጋፋችሁና በችሎታዎቻችን ላይ እምነት ስለሰጣችሁን በድጋሚ እያመሰገንን በአንድነት በኢስላማዊው የፋይናንስ ዓለም ውስጥ ጉልህ የሆነ ተፅዕኖ ማድረጋችንን እንቀጥላለን።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!!!
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
ሂጅራ ባንክ
ጉዞ ወደ ብሩህ ተስፋ!
Baankiin Hijraa jiraattota magaalaa Halabaa waliin Adoolessa 29/2015 tti marii bareedaa geggeesseera.
Marii isaanii keessatti Baankiin Islaamaa ija amantiitiin akkamitti akka ilaalamu irratti ibsi bal’aan kan kenname yoo ta’u, milkaa’ina baankichaaf gaheen hawaasaa guddaa akka ta’e ibsameera.
Gaaffilee hirmaattonni kaasan irrattis deebiin adda adda kennameera.
Dhumarrattis, Baankiin Hijraa bu’aa qabsoo hawaasaa ta’ee bu’aa caalu akka galmeessuuf qooda fudhattoonni hundi gahee isaanii akka bahatan waamicha dhiyeessuun mariin xumurame.
Baankii Hijraa
Imala gara egeree ifaa!
o.
Leave A Comment